የዞን ዘጠኝ ጉዳይ ዛሬም ውሳኔ ሳይሰጥ ቀረ

  • መለስካቸው አምሃ

ዞን ዘጠኝ

የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በኢንተርኔት አምደኞች በነሶሊያና ሽመልስና በአቃቤ ሕግ መካከል ባለው ክርክር ላይ ዛሬም ለስድስተኛ ጊዜ ውሳኔ ሳይሰጥ ቀርቷል፡፡

የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በኢንተርኔት አምደኞች በነሶሊያና ሽመልስ በአቃቤ ሕግ መካከል ባለው ክርክር ላይ ዛሬም ለስድስተኛ ጊዜ ውሳኔ ሳይሰጥ ቀርቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ ውሳኔው ለመስጠት ያለቻለው ከመዝገቡ ጋር መያያዝ የነበረባቸው ማስረጃዎች ተሟልተው የገቡት ዛሬ በመሆኑና መመርመር ያለባቸው ማስረጃዎችም ብዙ በመሆናቸው ነው ብሏል፡፡

የመልስ ሰጭዎቹ ጠበቃ ለውሳኔው መጓተት አንዱ ምክንያት ሆኖ የቀየው የCD ማስረጃ ደንበኞቻቸውን የማይመለከት መሆኑን ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የዞን ዘጠኝ ጉዳይ ዛሬም ውሳኔ ሳይሰጥ ቀረ