ብሊንከን በተባባሰው ጦርነት ከሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋራ ተወያዩ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከሊባኖሱ ከሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ነጂብ ሚካቲ ጋር ለንደን ተገናኝተዋል፡፡

ዋሽንግተን የቤይሩት መንግሥት በሂዝቦላ ላይ ክስ እንዲመሰርት ግፊት በምታደርግበት በአኹኑ ወቅት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ እስራኤል በሀገሪቱ ላይ ስላደረሰችው ጥቃት ከሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ዛሬ ዓርብ ውይይት አድርገዋል።

ብሊንከን ከአንድ ቀን በፊት በሊባኖስ ጉዳይ ፓሪስ ላይ በተካሄደው ጉባኤ ተካፋይ ከነበሩት ከሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ነጂብ ሚካቲ ጋር ለንደን ውስጥ የተገናኙት ከመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝት ሲመለሱ ነው።

ሁለቱ በካሜራዎች ፊት ፈገግ ሲሉ ቢታዩም ምንም አስተያየት አልሰጡም።

የእስራኤል ዋነኛ የፖለቲካ እና ወታደራዊ አጋር የሆነችው አሜሪካ እስራኤል ሊባኖስ ውስጥ በኢራን በሚደገፈው የሂዝቦላ ሚሊሻ ላይ ያነጣጠረ የአንድ ወር የቦምብ ጥቃት ባደረሰች ጊዜ አፋጣኝ የተኩስ አቁም ጥሪ አላቀረበችም።

ይሁን እንጂ ብሊንከን ለአፋጣኛ የዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ጥሪ አድርገዋል፡፡

ብሊንከን "ይህ ወደ ተራዘመ ዘመቻ እንዳያመራ ፣ሊያመራም እንደማይገባ እና እስራኤል በሰለማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ አለባት፣ የተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ ሃይሎችን ወይም የሊባኖስን ጦር ሃይሎችን አደጋ ላይ እንዳይጥል ማድረግም ይኖርባታል" ሲሉ ትላንት ሐሙስ ዶሃ ውስጥ ተናግረዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ለረጅም ጊዜ የዋለለውን የሊባኖስ ማዕከላዊ መንግሥት፣ ደህንነቱን የማስጠብቅ ኃላፊነት እንዲወስድ እና የራሱ የሆነ ጦር የመሰረተውን በኢራን የሚደገፈውን የሺዓ ንቅናቄ አራማጅ ሂዞቦላህን ትጥቅ እንዲያስፈታ ጥሪ አቅርባለች፡፡

እ.ኤ.አ ጥቅምት 7 ቀን 2023፣ የፍልስጤም ታጣቂዎች ያደረሱት ጥቃት፣ ያስከተለውን መጠነ ሰፊ የእስራኤል ወታደራዊ ጥቃት ተከትሎ፣ ሂዝቦላህ አጋርነቱን ለመግለጽ፣ ሚሳይሎችን ወደ እስራኤል ሲተኩስ ቆይቷል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ለእስራኤል አቻቸው ዮአቭ ጋላንት ባስተላለፉት ጥሪ ቢያንስ 11 የሊባኖስ ወታደሮችን የገደለው የእስራኤል ጦር ጥቃት እንዳሳሰባቸው ገልጿል።