ጥቁር አሜሪካዊያን ለአፓርታይድ መውደቅ ያደረጉት ትግል

ጄሲ ጃክሰን፣ ራንደል ራቢንሰን፣ ማክሲን ዋተርስ




የኔልሰን ማንዴላ የቀብር ሥነ-ሥርዓት


Your browser doesn’t support HTML5

ጥቁር አሜሪካዊያን ለአፓርታይድ መውደቅ ያደረጉት ትግል


በፅናትና በብልህነት፣ በይቅርባይነትና በትህትና ኑሮ መርተው ከጥቂት ቀናት በፊት ከዚህ ዓለም የተለዩት ኔልስን ማንዴላ በዘረኛው ሥርዓት ወኅኒ ተወርውረው ለረዥም ዓመታት ሲማቅቁ፣ ጥቁሩ ወገናቸው፤ ሴት፣ ወንድ፣ ወጣት፣ ሽማግሌ ሳይባል ሲገደልና ሲታሠር፣ ሥርዓቱ ወንጀሉን እንዲያቆም ለመናገር የደፈሩ የዓለም አገሮች ከኢትዮጵያና ሌሎችም የአፍሪቃ አገሮች በስተቀር እንደ ኩባና ሶቪዬት ሕብረት ያሉ ጥቂት ሶሻሊስት አገሮች ነበሩ።

ኔልሰን ማንዴላ

በዩናይትድ ስቴትስ ግን ማንዴላ ከእሥር ቤት እንዲፈቱ፣ በደቡብ አፍሪቃ እኩልነት እንዲሠፍን፣ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የጮኹና የነፃነቱን ትግል በዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ውስጥ ያቀጣጠሉ፣ የአፓርታይድ ሥርዓት የኢኮኖሚ ማዕቀብ ተጥሎበት እንዲንበረከክ ያስቻሉ፣ ጥቁር አሜሪካዊያን የሲቪል መብቶች መሪዎች ናቸው፡፡

ትዝታ በላቸው ያቀናበረችው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፤ ያዳምጡት፡፡