የሆራ ሀርሴዴ የኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ተከበረ

Your browser doesn’t support HTML5

የሆራ ሀርሴዴ የኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ተከበረ

የኦሮሞ ሕዝብ የምስጋና ጊዜ የሆነው የሆራ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል ዛሬ መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ/ም በቢሾፍቱ ከተማ ተከብሯል።

“ሆራ ሀርሴዴ ልዩ ክብር ያለውና የኦሮሞ ሕዝብ መስዋዕት የከፈለበት ቦታ ነው” ሲሉ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

የሆራ ፊንፊኔ እና የሆራ ሀርሴዴ ኢሬቻ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ እና በቢሽፍቱ

በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብና አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች እና ከጎረቤት ሀገራት የመጡ እንግዶች እንዲሁም የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች በበዓሉ መታደማቸውን የገለጸው ደግሞ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ነው።

ኮሚሽኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ “የሆራ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተጠናቋል” ሲል አስታውቋል።