ካለፉት 19 ዓመታት ወዲህ በድሃ ሀገሮች ሳይቀር የኑሮ ሁኔታ የተሻለ ቢሆንም በቢልዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ዕኩልነት በጎደለው ኑሮ እንደሚገኙ አንድ አዲስ ዘገባ ገልጿል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ተቋም ያወጣው ሦስተኛው ዓመታዊ ዘገባ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዘላቂ የልማት ግብን አብዛኞቹ ሀገሮች እአአ እስከ 2030 ባለው ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ቃል የገቡባቸውን 17 ዕርምጃዎችን አስመልክቶ ያወጣው ዘገባ ነው። እነዚህ ጥረቶች ብዙም እንዳልተራመዱ ዘገባው ገልጿል።
ብዙ መሻሽል እያሳየን ቢሆንም በብዙ ሀገሮች 10 ከመቶ የሚሆኑ ልጆች አምስት ዓመት ዕድሜ ሳይሞልቸው እየሞቱ መሆናቸውን ዘገባው አውስቷል። ይህ ሁኔታ የተሻለ ሥራ እንድንሰራ ማነሳሳት አለበት ብለዋል ቢል ጌትስ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ።