ባይደን ስለኮቪድ ዓለምአቀፍ ጉባኤ ይጠራሉ

  • ቪኦኤ ዜና
ፎቶ ፋይል፦ የኮቪድ 19 ክትባቶች

ፎቶ ፋይል፦ የኮቪድ 19 ክትባቶች

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የኮቪድ-19 ክትባቶችን አቅርቦት ለማሳደግ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ይጠራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የዩናይትድ ስቴትስ ዜና ማሰራጫዎች ዘገቡ፡፡

ጉባኤው በዚህ ወር መገባደጃ ላይ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ በሚደረግበት አካባቢ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ እንደዘገበው የመነጋገሪያ አጀንዳው የዓለም የጤና ቀውስን አስመልክቶና ሲሆን በታዳጊ አገሮች ያለውን የክትባት ስርጭት አድላዊነትና፣ ዘገምተኝነት ለማስወገድና በጋራ ለመቅረፍ እንዲቻል፣ በዓለም መሪዎች መካከል ያለውን ቅንጅት ለመፍጠር እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

ዩናትድ ስቴትስና ሌሎች የበለጸጉ አገሮች ወረርሽኙ በበረታባቸው ድሆቹ አገሮች የሚያደርጉት የኮቪድ 19 ክትባት ስርጭት እጅግ አነስተኛ በመሆኑ ከፍተኛ ወቀሳ እየተሰነዘረባቸው መሆኑን ይታወቃል፡፡