ጆ ባይደን አሸዋ ባዘለ ከረጢት ተደናቅፈው ወደቁ

  • ቪኦኤ ዜና

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ትላንት በአየር ሃይል አካዳሚ ምረቃ ሥነ ስርዐት ወቅት በሥፍራው በነበረ አሸዋ ያዘለ ከረጢት ተደናቅፈው ወደቁ።

ባይደን ድንገቱ በደረሰበት ወቅት ከኮሎራዶ ክፍለ ግዛቷ፡ የኮሎራዶ ስፕሪንግስ ከተማ ሥነ ስርዐቱ በመካሄድ ላይ ከነበረበት ሥፍራ ከመድረኩ ፊት ለፊት ቆመው የተመራቂዎችን እጅ በመጨበጥ ሰላምታ ከሰጡ በኋላ ወደ መቀመጫቸው በመመለስ ላይ ነበሩ። ወዲያውኑም በአንድ የአየር ኃይል መኮንን እና በሁለት ልዩ የፕሬዝዳንታዊ ጥበቃ አገልግሎት ሠራተኞቻቸው ድጋፍ ከወደቁበት በመነሳት ወደ መቀመጫቸው አምርተዋል።

የአሸዋ ከረጢት ጠቀለለኝ”

በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንቶች ታሪክ በዕድሜ ከሁሉ አንጋፋ የሆኑት የ80 ዓመቱ ባይደን የክብረ በዓሉን መጨረሻ ለመከታተል ከወደቁበት ተነስተው ወደ መቀመጫቸው ከመመለሳቸው በፊት፣ ለሥነ ስርዐቱ የተጋበዙትን ልዑካን አባላት ጨምሮ በሥፍራው የነበሩ ተመልካቾች ሁኔታውን በጭንቀት ሲመለከቱ ተስተውለዋል።

ፕሬዚዳንቱ አመሻሹ ላይ ወደ ዋይት ሃውስ እንደተመለሱ፤ ‘ዱብ-ዱብ’ በሚል ዓይነት እየተንቀሳቀሱ “የአሸዋ ከረጢት ጠቀለለኝ” ሲሉ ፈገግ ብለው ለጋዜጠኞች ስለድንገቱ ተናግረዋል።

ባይደን ከወደቁበት መድረክን አቅራቢያ ፕሬዚዳንቱ ለተመራቂዎች ያሰሙት ንግግር የሰፈረበትን መሳሪያ ለመደገፍ የተቀመጡ ሁለት አነስተኛ ጥቋቁር የአሸዋ ከረጢቶች ከመድረክ ላይ ነበሩ።