ባይደን በፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ዘመቻው እንደሚቀጥሉ በአጽንዖት ተናገሩ

  • ቪኦኤ ዜና

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሲናገሩ

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ትላንት ኀሙስ ምሽት፣ ለአንድ ሰዓት ገደማ በዘለቀው ጋዜጣዊ መግለጫቸው፣ በፕሬዚዳንታዊ ዘመቻቸው ለመቀጠል ያላቸውን ቁርጠኝነት ተናግረዋል።

ከጋዜጠኞች የአእምራቸውን ጤና በተመለከተ የተነሡ ጥያቄዎችን የተከላከሉት ባይደን፣ በተለይ በውጭ ፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ዝርዝር ምላሾችን ሰጥተዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

ባይደን በፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ዘመቻው እንደሚቀጥሉ በአጽንዖት ተናገሩ

ፕሬዚዳንቱ ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት፣ መሰንበቻውን በዋሽንግተን በተካሔደውና ዩክሬን በሩሲያ የተቃጣባትን ጥቃት ለመከላከል ያላትን ዐቅም ለማጠናከር ስለሚያግዙ ተጨባጭ ርምጃዎች፣ የአባል ሀገራት መሪዎች በተስማሙበት የኔቶ ጉባኤ መገባደጃ ላይ ነው።

የአሜሪካ ድምጿ የኋይት ሐውስ ዘጋቢ አኒታ ፓውል ከዋሽንግተን ያጠናቀረችውን ዘገባ፣ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።