ባይደን የአንጎላን የሎቢቶ ወደብ ጎበኙ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ከአንጎላ፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ ዛምቢያ እና ታንዛኒያ መሪዎች ጋራ በመሆን የሎቢቶን ወደብ ጎብኝተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ዛሬ ረቡዕ የአንጎላን የሎቢቶን ወደብ ጎብኝተዋል፡፡ የሎቢቶ ወደብ ወጪው በዩናይትድ ስቴትስ ወጪ የሚሸፈነው እና ከህንድ ውቂያኖስ እስከአትላንቲክ ተሻጋሪ ንግድ እንቅስቃሴዎችን ያጠናክራል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ረጅም የባቡር መስመር መዳረሻ ነው፡፡ ባይደን በቆይታቸው የአንጎላን ብሔራዊ የባሪያ ፍንገላ ዘመን መታሰቢያ ቤተ መዘክር ጎብኝተዋል፡፡

በሃሩን ማሩፍ የተጠናቀረው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፡፡ ቆንጅት ታየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ባይደን የአንጎላን የሎቢቶ ወደብ ጎበኙ