የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የኦነግን ባንዲራ በያዙ ታጣቂዎች ጥቃት እንደተከፈተበት አስታወቀ

በማኅበራዊ ሚዲያ ፌስቡክና ትዊተር ላይ አግኝተን በስክሪን ኮፒ የወሰድነው ፎቶ ግራፍ ነው።

የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) በበኩሉ ሠራዊቱ በእንደዚህ ዓይነት ተግባር ላይ እንደማይሰማራ አስታውቋል።

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አራት የካማሽ ዞን አመራሮች በታጣቂዎች መገደል የቀሰቀሰው ግጭት ለብዙ ሺዎች መፈናቀል ምንክኒያት ሆኗል ተብሏል።

የክልሉ መንግሥት በበኩሉ ከሰኔ 16/2010 ጀምሮ የተለያዩ ግጭቶች እየተፈጠሩ መሆኑን ገልፆ የአመራሮቹ በታጣቂዎች መገደል ደግሞ ነገሩን የበለጠ እንዳባባሰው ጠቁመዋል።

በአሁኑ ሰዓትም የፌደራልና የመከላከያ ሰራዊ አባላት ግጭቶቹ ወደ ተፈጠሩባቸው አምስት ወረዳዎች ገብተው በማረጋጋት ላይ እንደሆኑም ገልፀዋል።

ጥቃቱ በአምስት ወረዳዎች መድረሱን የሚናገሩት ነዋሪዎች በበኩላቸው ከአንዳንዶቹ ወረዳዎች ቀያቸውን ጥለው በመሰደድ ላይ እንደሚገኙ ሲናገሩ በአንዳንዶቹ ደግሞ ባሉበት አንድ ላይ መጠለያ ውስጥ ተሸሽገው እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የኦነግን ባንዲራ በያዙ ታጣቂዎች ጥቃት እንደተከፈተበት አስታወቀ

በካማሽ ጉዳይ የአርብ ምሽት ዘገባ

Your browser doesn’t support HTML5

በካማሽ ጉዳይ የአርብ ምሽት ዘገባ