አዲስ አበባ —
“በቤንሻንጉል ጉምዝ የተለያዩ ወረዳዎች ለሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ዕድሜ የሰጣቸው የአካባቢው መልክዐምድር እና የክረምቱ ወቅት ነው” ብለዋል የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይስሃቅ አብዱልቃድር ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል።
“በመከላከያና በፀጥታ አስከባሪዎች ከሚገደሉና ከሚማረኩ ታጣቂዎች ተገኘ” ያሉትን መረጃ የጠቀሱት አቶ ይስሃቅ በተከታታይ ለተፈፀሙት ጥቃቶች የጉምዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄንና ህወሃትን ተጠያቂ አድርገዋል።
አቶ ይስሃቅ አብዱልቃድርን በስልክ ያነጋገረው እስክንድር ፍሬው ነው፤ በመከላከያ አባላት ተገደሉ ያሏቸውን 14 ታጣቂዎች ጨምሮ ለሃያ ስምንት ሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆነውን ከትናንት በስተያ የተፈፀመውን ጥቃት ያብራራሉ።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5