በቤኒሻንጉል ጉምዝ በጥቃት በተጠረጠሩ ላይ ክሦች ተመሠረቱ

ፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በመተከል ዞን በተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ ግድያ፣ ማፈናቀል እንዲሁም ንብረት ማውደም ውስጥ እጃቸው አለበት ባላቸው ግለሰቦች ላይ ክሥ መመሥረቱን አስታውቋል።

ከተከሳሾቹ መካከል በየደረጃው ያሉ የአመራር አባላት እንደሚገኙበት የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የተደራጀና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ላፒሶ አመልክተዋል።

ፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ባሉ ቀበሌዎች ውስጥ በዘንድሮ ዓመት ብቻ በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ በደረሰው ግድያ መፈናቀልና ንብረት መውደም ተሳትፈዋል ባላቸው ቁጥራቸው 600 በሚጠጋ ግለሰቦች ላይ ክሥ መመሥረቱን አስታውቋል።

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተደራጀና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ላፒሶ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

በቤኒሻንጉል ጉምዝ በጥቃት በተጠረጠሩ ላይ ክሦች ተመሠረቱ