የኦሮምያ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የጋራ መድረክ

የኦሮምያ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የጋራ የህዝብ ለህዝብ መድረክ በጊምቢ ከተማ ተካሂዷል።

የሕዝቡን ሰላም የሚያውኩ ሰዎችን የመቆጣጠር ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በውይይቱ ላይ ተነግሯል።
ቪኦኤ ያነግገራቸው አንዳንድ የመድረኩ ተሳታፊዎች በአካባቢው የሚኖሩ የቤኒሻንጉል ጉምዝና የኦሮሞ ተወላጆች ሰላም ወደ ቀድሞ ሁኔታ ተመልሷል ብለዋል።
መድረኩ በምዕራብ ወለጋ ቡኖ በደሌና ካማሽ ዞኖች አዋሳኝ ቦታ ላይ መደረጉ የሦስቱን ዞኖች ነዋሪዎች ግንኙነት እንደሚያጠናክር የሁለቱ ክልሎች የጋራ ሰላምና ልማት ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ዲንሣ አመንቴ ገልፀዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የኦሮምያ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የጋራ መድረክ