ባህር ዳር —
በቤንሻጉል ጉምዝ ክልል ጉባ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖሩ የአማራ ብሄር ተወላጆች አሁንም ሥጋት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከትናንት በስተያ ማክሰኞ ጥቃት አድራሾች ሁለት ሰዎችን ከገደሉ በኋላ ውጥረት ሰፍኖ እንደነበረ የቀበሌዎቹ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።
በአካባቢው ፀጥታ አስከባሪዎች ቢኖሩም ከበላይ አካል ትዕዛዝ አልደረሰንም በማለት እርምጃ ሳይወስዱ መቅረታቸውን ነዋሪዎቹ አመልክተዋል።
ከቀናት በፊት ከአል መሀል ቀበሌ የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችም እስካሁን አለመመለሳቸውን ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5