ካማሺ ከተማን ከምዕራብ ወለጋ ጋር የሚያገናኘው መጓጓዣ ተቋርጧል

Your browser doesn’t support HTML5

ካማሺ ከተማን ከምዕራብ ወለጋ ጋር የሚያገናኘው መጓጓዣ ተቋርጧል

በቤኒሻንጉል ጉምዝ የካማሺ ከተማና በምዕራብ ወለጋ ዞን መካከል የመጓጓዣ አገልግሎት ከተቋረጠ ሣምንት ማለፉን አንዳንድ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ለቪኦኤ ተናግረዋል።

"አገልግሎቱ የተቋረጠው ባለፈው ሳምንት ውስጥ የዞኑ ማረሚያ ቤት ሦስት መኮንኖች በታጣቂዎች መታገታቸውን ተከትሎ በተፈጠረው የፀጥታ ሥጋት ነው" ብለዋል የካማሺ ዞን የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቡድን መሪ አቶ ጀርሞሳ ተገኘ።

"ታግተዋል” ያሏቸው ሰዎች እስከ አሁን አለመገኘታቸውንና የመጓጓዣ አገልግሎት እንዲጀመርም ከምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳደር ጋር እየተወያዩ መሆናቸውን አቶ ጀርሞሳ አክለው ገልፀዋል።