የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ /ኦፌኮ/ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ለዋስ መብታቸው መታገድ የሰጡት መልስ "ተገቢ ያልሆነና ሕግን ያልተከተለ ነው" ሲል ፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መልስ ሰጠ፡፡ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በአቶ በቀለ ላይ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ እንዲያፀናም ጠይቋል፡፡
አዲስ አበባ —
ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ለፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በፃፈው የመልስ መልስ ተጠሪው አቶ በቀለ ገርባ ፍርድ ቤቱ ለዋስትና መብታቸው በሰጠው እግድ ላይ የሰጡትን መልስ ‘ተገቢ ያልሆነና ሕግን ያልተከተለ ነው’ ብሎታል።
አቃቤ ሕግ በሰጠው መልስ እንደዘረዘረው ያቀረቡትን የዋስ መብት ጥያቄ ውድቅ ባደረገባቸው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት መደበኛ ያልሆኑት ዳኛ፣ ማለትም የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት በተሰየሙበት ችሎት መልሱን በማሰማታቸው አቶ በቀለ ገርባ ያነሱት ክርክር ‘የሕግ መሠረት የለውም’ ብሏል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔም ‘ፖለቲካዊ ነው’ ያሉት ‘ተገቢ ያልሆነና ሕግን ያልተከተለ በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው ነው’ ሲል አቃቤ ሕግ በማመልከቻው ተከራክሯል።
በመጨረሻም አቃቤ ሕግ የተጠሪን መልስ ውድቅ በማድረግ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎች የሰጠውን ውሣኔ በመሻር ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሣኔ እንዲያፀና አመልክቷል።
ሰበር ሰሚችው ችሎት በጉዳዩ ላይ ውሣኔ ለመስጠት ለታኅሣስ 17/2010 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5