ራያ ቢራ ፋብሪካ በማይጨው ከተማ አቅራቢያ ላሉ ገበሬዎች እስካሁን ከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ተረፈ-ምርት በእርዳታ መስጠቱን አስታውቋል፡፡
መቀለ —
በማይጨው ከተማ በአንድ ቢሊዮን ሰባት መቶ ሚሊዮን ቢሊዮን ብር መዋዕለ-ነዋይ የተቋቋመው የራያ ቢራ ፋብሪካ በደቡብ ትግራይ ያጋጠመውን የእንስሣት መኖ እጥረት ለመቋቋም የፋብሪካውን ተረፈ-ምርት ለገበሬዎች በነፃ እያከፋፈለ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ፋብሪካው እስካሁን ሦስት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሺህ ብር የሚገመት እርዳታ የሰጠ ሲሆን በዚህ ዓመት ሃያ ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ተረፈ-ምርት ለገበሬዎቹ በነፃ ለመስጠት አቅዷል።
ግርማይ ገብሩ ገበሬዎቹን አነጋግሮ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5