ዋሽንግተን ዲሲ —
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት ሱዳን ውስጥ ተቃዋሚዎች መገደላቸውን አውግዘዋል።
ከተገደሉት መካከል አስራ አምስቱ ትናንት ብቻ ካርቱም፥ ካርቱም ባህሪ እና ኡምዱርማን ውስጥ በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ በጥይት የተገደሉ መሆናቸውን ከሰብዓዊ መብት ኮሚሽነሯ ያወጡት መግለጫ አመልክቷል።
ለሱዳን የጦር ሰራዊት እና የጸጥታ ኃይሎች በተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ አላስፈላጊ እና ያልተመጣጠነ ኃይል እንዳይጠቀሙ በተደጋጋሚ ተማጽነናል፣ ያም ሆኖ ትናንትም እንደገና በሰልፈኞች ላይ ጥይት መተኮሳቸው አሳፋሪ አድራጎት ነው ሲሉ የተመድ ሚሼል ባሽሌት አውግዘዋል።