ከስድሳ በመቶ በላይ ኢትዮጵያውያን በከፋ ድህነት ውስጥ መውደቃቸው ተጠቆመ

Your browser doesn’t support HTML5

ከስድሳ በመቶ በላይ ኢትዮጵያውያን በከፋ ድህነት ውስጥ መውደቃቸው ተጠቆመ

“አፍሮ ባሮ ሜትር” የተባለ የጥናት እና የምርምር ተቋም ባካሔደው የዳሰሳ ጥናት፣ 61 በመቶ ያህል ኢትዮጵያውያን በከፋ ድህነት ውስጥ መሆናቸውን አመላክቷል፡፡

በኢትዮጵያ የተቋሙ ተወካይ እና የጥናቱ ተመራማሪ አቶ ሙሉ ተካ፣ ጥናቱ፥ በአገራዊ ኢኮኖሚ፣ በግል የኑሮ ሁኔታ እና በድህነት ልኬት ላይ አተኩሮ መደረጉን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

በመላ አገሪቱ እንደተካሔደ በተገለጸው የዳሰሳ ጥናት፣ 65 በመቶ ኢትዮጵያውያን በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ደስተኛ እንዳልሆኑና ይሻሻላልም ብለው ተስፋ እንደማያደርጉ ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ሥራ ትምህርት ቤት መምህር ዶክተር ዳኪቶ ዓለሙ፣ የዳሰሳ ጥናቱ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ማመላከቱን ተናግረው፣ መንግሥት የዋጋ ንረቱን ጨምሮ ኢኮኖሚያዊ ልማቱ በሚሻሻልበት ሁኔታ ላይ ሊሠራ እንደሚገባ መክረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።