በቻግኒ ከተማ ግጭት አምስት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በቻግኒ ከተማ ግጭት አምስት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ቻግኒ ከተማ፣ ከጸጥታ ኀይሎች ጋራ ተፈጠረ በተባለ ግጭት፣ አምስት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች እና የከተማው ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ተቃዋሚው የአገው ብሔራዊ ሸንጎ ባወጣው መግለጫ፣ ሰዎቹ የተገደሉት፥ የመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች በወሰዱት የዘፈቀደ ርምጃ መኾኑን በመግለጽ ወንጅሏል። የከተማው አስተዳደር በበኩሉ፣ የሰዎቹ ሕይወት የጠፋው፣ በእገታ ወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ጥረት ሲደረግ፣ “ተጠርጣሪዎቹ ተኩስ በመክፈታቸው ነው፤” ሲል፣ ክሱን አስተባብሏል።