በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ተደጋግሞ በሚደርሰው ርዕደ መሬት ነዋሪዎች ስጋታቸውን ገለጹ

ፎቶ ፋይል፦ ሰመራ፣ አፋር

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ተደጋግሞ በሚደርሰው ርዕደ መሬት ምክንያት ሥጋት ውስጥ መውደቃቸውን የአካባቢው ኗሪዎች አስታወቁ፡፡

ትናንት እና ከትናንት በስቲያ ምሽት አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ተፈጠረ በተባለው ርዕደ መሬት የፈንታሌ ተራራ አናት ላይ የጭስ ምልክት ታይቷል፣ የከባድ ፍንዳታ ድምጽ ተሰምቷል፣ የድንጋይ ናዳም ተስተውሏል ሲሉ ኗሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ተደጋግሞ በሚደርሰው ርዕደ መሬት ነዋሪዎች ስጋታቸውን ገለጹ

ርዕደ መሬቱ የተፈጠረበት በአፋር ክልል ዞን ሦስት አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ወሃና ፍሳሽ አገልግሎት የመሬት መንቀጥቀጡንና ንዝረቱን ተከትሎ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቁ የአርብቶ አደሮች ፍየሎችና ግመሎች በድንጋጤ በርግገው መጥፋታቸውን ጠቁሟል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊሲክስ ህዋ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም በበኩሉ ላለፉት ስድስት ቀናት የመሬት መንቀጥቀጡ መከሰቱን አረጋግጦ የትናንቱ በሬክተር ስኬል 4.9 እንደሚለካ አመልክቷል፡፡