የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል፡፡
አዲስ አበባ —
የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ከፍተኛው ኃላፊነት ከመጡ የመጀመሪያቸው የሆነውን የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ያስተናግዳሉ፡፡
የኢትዮጵያው መሪ አጋጣሚውን የሕብረቱ አባልና መሥራችና መቀመጫ በሆነችው ሀገር እየተካሄደ ስላለው ለውጥ ለማብራራት እንደሚጠቀሙበት የጠ/ሚኒስትር የፕሬስ ኃላፊ ንጉሡ ጥላሁን ተናግረዋል፡፡
ጉባዔው ስለኢትዮጵያ ለውጥ ሂደት፣ ስኬትና ፈተናዎች ለማስገንዘብ መልካም ዕድል ነው ሲሉ ነው ያብራሩት፡፡
የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ኃላፊ (ፕሬስ ሴክሬታሪ) የሆኑትን አቶ ንጉሡ ጥላሁንን አነጋግረናቸዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5