የአፍሪቃ ህብረት ከሁለት ሳምንትት በፊት ባካሄደው ጉባኤ አለም አቀፍ የወንጀል ችሎት በሙዐማር ጋዳፊ ላይ ያወጣውን የእስራት ማዘዣ እንደማይቀብልና ከችሎቱ ጋር እንደማይተባበር ማስታወቁ ይታወቃል። የሊብያ ችግር በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታም እቅድ አቅርቧል። ስለ ጉዳዩ እንዲያብራሩልን ዶክተር መሰረት ቸኮልንና ዶክተር አየለ በከሬን አነጋግረናል።
"የአፍሪቃ ህብራት የአለም አቀፉን የወንጀል ችሎት የእስራት ማዘዣን የማይቀበለው በሊብያ ያለው የፖለቲካ ቀውስ የሚያስፈልገው የፖለቲላ መፍትሄ ነው። ስለሆነም የአፍሪቃ ህብረት ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት እየሰራ ነው። የወንጀሉ ችሎት የእስራት ማዛዣም የፖለቲካ መፍትሄ እንዳይመጣ እንቅፋት የሆነና ፍርድ ቤት ከመቅረብ በፊት ያለፈ ውሳኔ ነው በሚል ተቃወመው እንጂ ጋዳፊ ለፍርድ አይቅረቡ አላለም" ሲሉ ዶክተር አየለ አብራርተዋል።
ዶክተር መስረት ቸኮል ደግሞ "እርግጥ የሊብያ ጉዳይ የፖለቲካ መፍትሄ ያስፈልገዋል። ነገር ግን ጋዳፊ ብቻ አይደሉም ሊብያ ማለት። የተለያዩ የሊብያ ጎሳዎች በአንድነት ስምምነት ላይ የሚደርሱብት የፖለቲካ መፍትሄ ጋዳፊን ሳይጫመር ሊመጣ ይችላል። ስለሆነም የአፍሪቃ ህብረት ያለውን አልደግፍም" ብለዋል።