ሊብያ ውስጥና በሌሎችም የዓለም ክፍሎች መውጫ አጥተው የሚገኙ ዜጎቻቸውን ለመመለስ የናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ሙሐማዱ ቡሃሪ ቃል ገቡ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ሊብያ ውስጥና በሌሎችም የዓለም ክፍሎች መውጫ አጥተው የሚገኙ ዜጎቻቸውን ለመመለስ የናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ሙሐማዱ ቡሃሪ ቃል ገብተዋል።
ሚስተር ቡሃሪ ዜጎቻቸውን ለመመለስ ያሰቡት የሃገራቸውን ማኅበራዊና ምጣኔኃብታዊ መርኃግብሮችን በማስፋት እንደሆነ ተናግረዋል።
ቡሃሪ ይህንን ያሳወቁት አይቮሪ ኮስት ውስጥ ለተሰበሰቡ የአፍሪካና የአውሮፓ መሪዎች ነው።
የዚህ ስብሰባ ዋነኛ አጀንዳ የፍልሰት ጉዳይ ሲሆን በተለይ ሊብያ ውስጥ በባሪያ ፍንገላ ገበያ ላይ ምንጫቸው የምዕራብ አፍሪካ ሃገሮች የሆኑ ፍልሰተኞች ሲሸጡ የሚያሳይ ቪድዮ በመገናኛ ብዙኃን ከወጣ ወዲህ ጉዳዩ የመሪዎቹን ትኩረት ሙሉ በሙሉ መሳቡ ተነግሯል።
በስብሰባው ላይ ከተናገሩት መካከል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ የፍልሰትን ጉዳይ አጥብቆ የመያዝን ፈተናዎችና ዕድሎች ጠቋቁመዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5