የአፍሪካ ህብረት 110 ሚሊዮን የሞደርና ክትባት መድሃኒቶችን ሊገዛ ነው

  • ቪኦኤ ዜና
የአፍሪካ ህብረት ዋና መሥሪያ ቤት - አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

የአፍሪካ ህብረት ዋና መሥሪያ ቤት - አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

የአፍሪካ ህብረት እስክ 110 ሚሊዮን የሞደርና ክትባት መድሃኒቶችን እንደሚገዛ የሮይተርስ ዘገባ አመለከተ፡፡

ህብረቱ ወደ 15 ሚሊዮን የሚጠጋ የክትባት መድሃኒቶችን ይህ የአውሮፓውያን ዓመት ከመገባደዱ በፊት የሚያገኝ ሲሆን ቀሪዎቹን እኤአ እስከ 2022 አጋማሽ ላይ እንደሚያገኛቸው ተመልክቷል፡፡

የግዥው ሥምምነት የተመቻቸው፣ በፕሬዚዳንት ባይደን አስተዳደር ሲሆን፣ ሞደርና በድርድሩ ከህብረቱ ጋር እንዲስማማ ዩናይትድ ስቴትስ ለአፍሪካ ህብረት ከሞደርና የገዛቸውን 33ሚሊዮን የክትባት መድሃኒቶች ማዘግየቷን ተከትሎ መሆኑም ተነገሯል፡፡

የአፍሪካ ህብረት የኮሮናቫይረስ ልኡክ ስትራይቭ ማሲያዋ “ይህ የሚያስፈልገንን የክትባት መጠን በአሰቸኳይ ለመጨመር በጣም አስፈላጊያችን ነው፤ ሌሎች የክትባት አምራች አገሮችም የዩናይትድ ስቴትስን መንግሥት አርአያ ተከትለው ተመሳሳይ ግዥ እንድንፈጽም ቢተባበሩን መልካም ነው” ማለታቸውን ሮይተር ዘግቧል፡፡