ኃይለኛ ንፋስ የቀላቀለ ዝናም ያዘለው ፍሎረንስ የተሰኘው አውሎ ንፋስ፣ ሰሜንና ደቡብ ካሮላይና ግዛት ውስጥ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱ ተገለጸ። እስካሁን ቢያንስ አምስት ሰዎች ሞተዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
አውሎ ንፋሱ ባደረሰው የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ በአሁኑ ሰዓት መብራት እንደሌለውና ከቤት ንብረቱ መፈናቀሉም ታውቋል።
የብሔራዊ ሄሪከን ማዕከል ዛሬ ቅዳሜ እንዳስጠነቀቀው፣ ማዕበሉ አሁንም እየጨመረና ሌላም ጥፋት እያደረሰ ነው።