ሠላሳ ኢትዮጵያውያንና ሶማልያውያን ፍልሰተኞች በየመን የባሕር ወደብ ሰጥመው ሞቱ

  • ቪኦኤ ዜና
ሁለት የተመድ የረድዔት ሠራተኞች ዛሬ ባወጡት መግለጫ፣ በዚህ ሳምንት መግቢያ በየመን የባሕር ወደብ በሰጠሙት ሠላሳ ፍልሰተኞች ሞት የተሰማቸውን ኃዘን ገለጹ።

ሁለት የተመድ የረድዔት ሠራተኞች ዛሬ ባወጡት መግለጫ፣ በዚህ ሳምንት መግቢያ በየመን የባሕር ወደብ በሰጠሙት ሠላሳ ፍልሰተኞች ሞት የተሰማቸውን ኃዘን ገለጹ።

መግለጫ ያወጡት ሁለቱ ድርጅቶች፣ ዓለማቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት /አይኦኤም/ እና የተመድ የስደተኞች መሥሪያ ቤት ናቸው።

አደጋው የደረሰባቸው 152 ፍልሰተኞች ከሶማልያና ከኢትዮጵያ ሲሆኑ፣ አሸጋጋሪዎች በጂቡቲ በኩል ይዘዋቸው ሊወጡ መሞከራቸው ተገልጧል።

እአአ 2017 ወደ የመን ለመዝለቅ የሞከሩ ከ87 ሺህ በላይ ፍልሰተኞች ለአደጋ መጋለጣቸው ይታወቃል።