የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን፤ እንዲሁም የቡና፣ የመድንና የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለቦች ተሠላፊ የነበረው አሰግድ ተስፋዬ ዛሬ /ቅዳሜ ግንቦት 26/2009 ዓ.ም./ ረፋድ ላይ በድንገት አርፏል፡፡
አዲስ አበባ —
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን፤ እንዲሁም የቡና፣ የመድንና የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለቦች ተሠላፊ የነበረው አሰግድ ተስፋዬ ዛሬ /ቅዳሜ ግንቦት 26/2009 ዓ.ም./ ረፋድ ላይ በድንገት አርፏል፡፡
አሰግድ ወድቆ ሕይወቱ ያለፈው አዲስ አበባ ውስጥ በተለምዶ የቀበሌ ሃያ ሦስት ሜዳ ተብሎ በሚጠራው ሜዳ ላይ ለሰውነት ማነቃቂያ ተጫውቶ ከጨረሰ በኋላ ሰውነቱን ታጥቦ ሲወጣ እንደሆነ በሥፍራው የነበሩ ጓደኞቹ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡
የአሰግድ አስከሬን ወዲያው ለምርመራ ወደ ዳግማዊ ምንልክ መታሰቢያ ሆስፒታል መወሰዱና የምርመራ ውጤት እየተጠበቀ መሆኑ ታውቋል፡፡
አሰግድ በቅርቡ ከመሠረተው ትዳር አንድ ልጅ ማፍራቱ ተገልጿል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5
የእግር ኳስ ተጫዋቹ አሰግድ ተስፋዬ አረፈ