ከስልጣናቸው የተባረሩት የሶሪያ ፕሬዝዳንት በሽር አል-አሳድ ሞስኮ መግባታቸውን በመግለፅ፣ የሩሲያ መንግስት መገናኛ ብዙሃን ሞስኮ ለአሳድ ጥገኝነት መስጠቷን ዘግበዋል። አሳድ በስልጣን ላይ እያሉ ታጣቂዎችን ለማሸነፍ ባደረጉት ትግል ክሬምሊን ቁልፍ የመንግስታቸው ደጋፊ የነበረች ሲሆን፣ ሞስኮ በሶሪያ የነበራትን፣ ከጥቂት ቀናት በፊት የማይነቃነቅ ይመስል የነበረ የበላይነት መልሶ ለማግኘት ግን አዳጋች ሊሆንባት ይችላል።
ሪካርዶ ማርኪና በዚህ ዙሪያ ያደረሰንን ዘገባ፣ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።