Your browser doesn’t support HTML5
የምናየው የቀለም አይነት በግልጽ እስከታየን ድረስ በእርግጠኝነት መናገር ብዙም አያዳግትም። ይሁንና ቁጥሩ በግምት ስምንት በመቶ ለሚደርሰው ሕዝብ ግን እውነታው የተለየ ነው። ቀለማት ተቀላልቅለው በሚታዩበት ምስል ውስጥ አጥርተን የማናየው የቀለም ዓይነት፣ ምስሉ ከምናየው የተለየ ሊኾን ይችላል።
በዚያ ላይ ችግሩ እንዳለ የምናውቅበት አጋጣሚ እስኪፈጠር ድረስ፣ ችግሩን ላናውቅ የምንችልበት አጋጣሚ አለ። በተለይ በወንዶች ላይ የሚከሰተውን ይህን ሁኔታ ምንነት እንዲያስረዱን ለዛሬ ሀኪሞን ይጠይቁ ፕሮግራም ዶ/ር ትልቅ ሰው ተሾመ ጋብዘናል።