የእስያና የአውሮፓ የአክስዮን ገበያዎች ዛሬ ወርደዋል። ይሁንና ትላንት በዩናይትድ ስቴትስ የአክስዮን ገበያ ላይ የታየውን ያህል አላሽቆለቆሉም።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የእስያና የአውሮፓ የአክስዮን ገበያዎች ዛሬ ወርደዋል። ይሁንና ትላንት በዩናይትድ ስቴትስ የአክስዮን ገበያ ላይ የታየውን ያህል አላሽቆለቆሉም። አሜሪካና ቻይና የሚያካሄዱት የንግድ ጦርነት እንዲሁም ፕረዚዳንት ትረምፕ በድረ-ገጽ በሚደረገው ግብይት ላይ የቃላት ጥቃት መሰንዘራቸው ለአክስዮን ዋጋ መቀነስ ምክንያት ሆነዋል የሚል ስጋት አለ።
ፕረዚዳንት ትረሞፕ በድረ-ገጽ ግብይት ስራው ግዙፍ የሆነውን አማዞን በጥቂት ቀናት ውስጥ ሶስት ጊዜ ነቅፈዋታል። የአማዞን መስራች Jeff Bezos የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ባለቤትም ነው። ጋዜጣው ስለ ትረምፕና አስተዳደራቸው የሚያቀርባቸው ዘገባዎች ፕረዚዳንቱን ያበሳጫሉ።