ኮቪድ-19 በእስራኤል

በእስራኤል ለሦስት ሳምንታት እንዲቆይ የተጣለው የእንቅሳሴ ገደብ ዛሬ ዓርብ ተጀመረ።

እስራኤል በሃገሪቱ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተጠቂዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ፣ በየቀኑ ወደ አምስት ሺ የሚደርሱ ሰዎች በቫይረሱ እየተጠቁ መምጣቻቸው ተዘግቧል፡፡ በዚህ የተነሳም በእስራኤል መንግሥት ለሦስት ሳምንታት እንዲቆይ የተጣለው የእንቅሳሴ ገደብ ዛሬ ዓርብ ተጀምሯል፡፡

በርካታ ሆስፒታሎች ለአዳዲስ የኮሮናቫይረስ ህሙማን የሚሆን የማስተማሚያ አልጋ የሌላቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ቫይረሱ በመላው ሃገሪቱ የተሰራጨ መሆኑ ቢነገርም፣ የአጥባቂ ኦርቶዶክስ አይሁድ አማኞችና የእስራኤል አረብ ማኅበረሰብ አባላት፣ በከፋ ሁኔታ የተጠቁ መሆናቸው ተዘግቧል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

Your browser doesn’t support HTML5

ኮቪድ-19 በእስራኤል