የሳምንቱ መገባደጂያ የእሁድ ምሽት የመዝናኛ ምርጫችሁ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ።
ዝነኛዋ ድምፃዊት ጂጂ፥ እጅጋየሁ ሽባባው፥ ስለ ሙዚቃና ህይወት እያወጋችንና ከዜማዋም ከእንጉርጉሮውም እያለች አብራን ታመሻለች።
ለወራት ተቋርጦ በመቆየቱ ሲያጋግር የከረመው፥ የዋሽንግተኑ ጣይቱ የባህል ማዕከል ወርሃዊ ዝግጅቱን ጀምሯል። የየካቲት ወሩን የፍቅር ቀን ተንተርሶ ከቀረቡ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች አንዱን ይዘናል።
«የተጨቆኑ ቀልዶች፤» በተሰኘው ዲቪዲ ዙሪያ የተደረገ ውይይትና የሳምንቱ ምርጥ ግጥም በመልክ በመልኩ ተሰናድተዋል።