«ሳውዲ አረቢያ በዚያች አገር ላሉ ለሚሊዮኖች ክርስቲያኖች የእምነት ነጻነት እየነፈገች ነው። በሃይማኖታቸው ሳቢያን ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን እያዋከበች ነው። ክርስቲያኖች መጽሃፍ ቅዱስ ይዘው በመገኘታቸው ብቻ በደል ይፈጸምባቸዋል። ይሄ የአሜሪካንም ሆነ የዓለም አቀፍ መሠረታዊ የሃይማኖት ነጻነት የሚጻረር ነው።»
ለበርካታ ወራት በሳውዲ አረቢያ ያለፍርድ የታሰሩ ከሰላሳ በላይ ኢትዮጵያዉያን የክርስትና እምነት ተከታዮችን ለማስፈታት የታለመ ሰላማዊ ሰልፍ በዛሬው ዕለት እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ተካሄዷል።
ከዋሽንግተኑ የሳውዲ ኤምባሲ ደጃፍ ለሦሥተኛ ጊዜ የተካሄደውን ሰልፍ የጠሩት በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በዓለም ዙሪያ በአማንያን ላይ የሚፈጸሙ በደሎችን ለመዋጋት የቆመ አንድ መቀመጫውን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገ የሰብዓዊ መብት ድርጅት በመተባበር ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ እዚያው ሳውዲ ዐረቢያ ውስጥ ባሉ በርካታ እስር ቤቶች ውስጥ «ያለ ፍትሃዊና በቂ የፍርድ ሂደት እአማቀቅን ነን፤ ስቃዩን ተሸክመናል፤» የሚሉ በእስር ቤቶች ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ብሶታቸውን ገልጸውልናል።
የዘገባዎቹን ሙሉ ዝርዝር ቀጥሎ ያድምጡ፤