ተከሳሾች ፍርድ ቤት ከመቅረባቸው በፊት ስቃይ እንደተፈጸመባቸው ተናገሩ

  • መለስካቸው አምሃ

በእነ አቶ አንዱዓለም አራጌ የክሥ መዝገብ የቀረቡ ተከሣሾች መከላከያቸውን ማሰማት ቀጥለዋል። አንዳንዶቹ ፍርድ ቤት ከመቅረባቸው በፊት ለወራት መታሰራቸውንና የማሰቃየት ተግባር እንደተፈጸመባቸው ለችሎቱ ገልፀዋል።