ኢትዮጵያ ኤርትራን አስመልክቶ አዲስ የውጭ ፖሊሲ ማውጣቷን ገለፀች። የአሥመራን መንግሥት ከሥልጣን ለማስወገድ "አስፈላጊውን ሁሉ አደርጋለሁ" አለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳመለከቱት የኤርትራን መንግሥት ከሥልጣን ለማውረድ መንግሥታቸው ዲፕሎማሲያዊም ሆነ ወታደራዊ እርምጃዎችን ይወስዳል።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ዲና ሙፍቲ ትላንት ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሰጡት ቃል «ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በኤርትራ ላይ አንድ እርምጃ እንዲወስድ ኢትዮጵያ ላደረገችው ተማጥኖ 'ጆሮ ዳባ ልበስ' በማለቱ ነው አሁን ጠበቅ ያለ አቋም ለመውሰድ የወሰነው» ሲሉ ይህንኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሃሣብ አፅንተው ተናግረዋል።
አምባሣደር ዲና በመግለጫቸው ኤርትራ ኢትዮጵያንና የተቀረውን የአፍሪቃ ቀንድ እንደእርሣቸውም አገላለፅ ”በማናጋቱ” ከቀጠለች መንግሥታቸው ቀጥተኛ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ አስጠንቅቀዋል።
ዝርዝሩን ከዘገባው ያድምጡ።