በአርሲ ተፈፀመ በተባለ ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች መገደላቸውን የተጎጂ ቤተሰቦች ተናገሩ

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሸርካ ወረዳ፣ ሐሙስ ኅዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም. በታጣቂዎች ተፈፀመ በተባለ ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች መገደላቸውን የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የተጎጂ ቤተሰቦች ገለጹ። ድርጊቱን የፈጸሙት “ሸኔ” ብለው የጠሯቸው ታጣቂዎች መኾናቸውን የተናገሩት ቤተሰቦች፣ በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች በአንድ ጉድጓድ ውስጥ፣ አርብ ኅዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም. በአንድ ላይ እንደቀበሯቸው ገልጸዋል። እናት ፓርቲ ድርጊቱን በጽኑ አውግዟል።

Your browser doesn’t support HTML5

በአርሲ ተፈፀመ በተባለ ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች መገደላቸውን የተጎጂ ቤተሰቦች ተናገሩ

ዕድሜው 44 ዓመት የኾነ ታናሽ ወንድማቸው በጥቃቱ እንደተገደለባቸው፣ ለቪኦኤ የተናገሩት አቶ አደበቡ ወርቅነህ፣ "የተፈጸመው ጥቃት ዘግናኝ ነው" ብለውታል። የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በጥቃቱ ውስጥ እጁ እንደሌለበት ገልጿል። ከፌደራልና ከክልሉ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።