ኦሮሚያ ውስጥ ተቃዋሚዎች በውጭ ኩባኒያዎች ላይ ጥቃት ሲከፍቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠር መዋዕለ ነዋይ ወደ ጭስነትና አመድነት ወርዷል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ከዚያ ሁከት በኋላ በመላ ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ታውጇል።
በአካባቢው ያለ አንድ ኩባንያ በማህበረሠብ መሪዎች እገዛና እርብርብ ከጥቃት ሊተርፍ ችሏል።
ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ወደ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፤ ማራንኬ ፕላንትስ ኩባንያ ።
የማራንኬ ፕላንስ ባለቤት ማርክ ድሪሰን ላለፉት 13 ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋይ አፍስሰው ሲሠሩ የኩባንያቸው መፃዒ ደህንነት ጉዳይ አሳስቧቸው እንደማያውቅ ተናግረዋል።
ባለፈው መስከረም 24 የተፈጠረው ሁኔታ ግን ያንን የመተማመኛቸውን ስሜት ቀይሮታል።
በአካባቢያቸው የነበሩ ብዙ ቁጥር ያላቸው ኩባንያዎች በእሳት ሲጋዩ አይተዋል።
የሁከቱ መጠን እያደገ፣ የሰው ቁጥርና ጩኸቱ እየበረከተ ሲመጣ ቀጣዩ የእርሳቸው ኩባንያ እንደሆነ መረዳታቸውን ይናገራሉ።
ማራንኬ ፕላንትስ ለውጭ ገበያ የሚላክ አበባ የሚያመርት ተቋም ነው።
ሪፖርተራችን ማርተ ፋን ዳር ቮልፍ ሰሞኑን ወደ አርሲ ዞን ዶኒ ከተማ ተጉዛ ነበር፤ ዘገባ አጠናክራለች ሰለሞን አባተ ያቀርበዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5