ዋሺንግተን ዲሲ —
Your browser doesn’t support HTML5
ህገ-ወጥ የተባሉና ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ከሦስት መቶ በላይ ስደተኞች ፍርዳቸውን ጨርሰው ነገር ግን አሁንም ማላዊ ውስጥ በቁጥጥር ስር መሆናቸው ተገልጿል።
ማረፊያ ቤት የሚቆዩት ወዳገራቸው ለመላክ ያለው ዝግጅት እስከሚጠናቀቅ መሆኑን የማላዊ መንግሥት ባለሥልጣናት ይናገራሉ።
የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ግን ሰዎች ፍርዳቸውን ከጨረሱ በኋላ እሥር ቤት ማቆየት ህገወጥ አሠራር ነው» ይላሉ።
ለዝርዝሩ ከብላንታየር የተጠናቀሩና አዲሱ አበበ ወደ ማላዊ እንዲሁም ናይሮቢ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደውሎ ያገኛቸውን መረጃዎች ያካተተበትን የተያያዘውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡