ደቡብ ሱዳን ውስጥ ጋዜጠኛን በመግደልና ባለፈው ዓመት አምስት ዓለምቀፍ የረድኤት ሠራተኞች ላይ የወሲብ ጥቃት በመፈጸም የተከሰሱ ወታደሮችን ይቆጣጠሩ የነበሩት የደቡብ ሱዳን ወታደራዊ መኮንን በእስር ቤት እንደሞቱ የሀገሪቱ ወታደራዊ ኃይል ገልጿል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ደቡብ ሱዳን ውስጥ ጋዜጠኛን በመግደልና ባለፈው ዓመት አምስት ዓለምቀፍ የረድኤት ሠራተኞች ላይ የወሲብ ጥቃት በመፈጸም የተከሰሱ ወታደሮችን ይቆጣጠሩ የነበሩት የደቡብ ሱዳን ወታደራዊ መኮንን በእስር ቤት እንደሞቱ የሀገሪቱ ወታደራዊ ኃይል ገልጿል።
ተቀዳሚ ሌተናንት ሉካ አከቻክ በታሰሩበት ክፍል ሞተው የተገኙት ከአንድ ሳምንት በፊት ሲሆን ይፋ የተደረገው ግን ባለፈው አርብ ነው።
ሉካ አከቻክ የሞቱት በተፈጥሮአዊ ምክንያት ነው ሲሉ የወታደራዊው ኃይል ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሳቶ ዶሚክ ተናግረዋል።
ሉካ አከቻክ ባለፈው አመት ጁባ በሚገኘው የተረይን ሆቴል ህንፃ ውስጥ በዕዛቸው ሥር የነበሩ ወታደሮችን የረድኤት ሠራተኞች ላይ የወሲብ ጥቃት እንዲፈጽሙ አዘዋል የሚል ክስ ከአንድ የወንጀሉ ሰላባ መሰማቱ ተገልጿል።