የዓረና ፓርቲ መግለጫ

የዓረና ለሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል። በስብሰባውን የፓርቲው የስድስት ወራት አፈፃፀምና ወቅታዊ ሀገራዊ ፓለቲካዊ ሁኔታም መገምገሙን የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምዶም ገብረሥላሴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

የዓረና ለሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል። በስብሰባውን የፓርቲው የስድስት ወራት አፈፃፀምና ወቅታዊ ሀገራዊ ፓለቲካዊ ሁኔታም መገምገሙን የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምዶም ገብረሥላሴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በውይይቱ በሀገሪቱ ለፓለቲካዊ እንቅስቃሴ የሚመች ሁኔታ መፈጠር ጀምሯል፣ በአንፃሩ ግን በትግራይ ይህ አካሄድ የዘገየ መሆኑን ገምግመዋል።

በአንድ አንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚታዩ ብሄር ለይተህ ጥቃት መፈፀምና የመንጋ ፍትህ አካሄድ ፓርቲው እንደሚያወግዘውም አንስተዋል።

በኢትዮ ኤርትራ የሰላም ሂደት አስመልክቶ ሥራ አስፈፃሚው መወያየቱ ያነሱት አቶ አምዶም የሰላም ሂደቱ ፓርቲው እንደሚደግፈውና እንዲሁም ይህ የሰላም ሂደት ሕዝብ ባማከለ መንገድ መፈፀም እንዳለበት ያምናል ብለዋል።

በዶ/ር አረጋዊ በርኸ የሚመራ የትግራይ ዴሞክራስያዊ ትብብር ፓርቲ፣ ውህደት ወይም ግንባር ለመፍጠርም ውይይት ተጀምሯል ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

Your browser doesn’t support HTML5

የዓረና ፓርቲ መግለጫ