የቀናቱ አብዮቶችና አንድምታቸው በባለሙያዎች በተከታታይ ይገመገማሉ፡፡
ለውጥ ፈላጊው የቱኒዚያ ሕዝብ ባለፈው ሣምንት አደባባይ ወጥቶ ቁጣውን የገለፀበት የተቃውሞ ሠልፍ ፕሬዚደንቱን ቤን አሊን ከነቤተሰባቸው አገር ጥለው እንዲሸሹ አስገድዷል።
በግብፅ ተመሣሣይ ሕዝባዊ ቁጣ ተቀጣጥሎ ለሰላሣ ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየውን የፕሬዚደንት ሆስኒ ሙባረክ መንግሥት አፍርሷል።
በሠላም ሥልጣን ካላስረከቡ ከቤን አሊ የተለየ ዕጣ እንደማይጠብቃቸው ግልፅ እየሆነ ነው።
በዮርዳኖስም በቱኒዚያና ግብፅ ሕዝቡ የመንግሥት ለውጥ ጥያቄ በማንሣት አደባባይ ወጥቷል። በሱዳንም አንዳንድ የለውጥ ፍለጋ ፍንጮች እየታዩ ነው፡፡
በአገሮቹ እየናረ የመጣው የምግብ ዋጋና የባለሥልጣናቱ በሙስና መዘፈቅ ሕዝብን አስቆጥቷል።
ይህ በሰሜን አፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ እንደ ሰደድ እሳት እየተያያዘ ያለው ሕዝባዊ አመፅ ቀጥሎ ወዴት ያመራል?
በሌሎች የአፍሪቃ አምባገነን መንግሥታትስ ላይ ተመሳሳይ ሁኔታ ሊቀሰቅስ ይችል ይሆን?
ለዛሬው ዝግጅት ሰለሞን ክፍሌ አቶ ስዬ አብርሃን አነጋግሯል፤ ያድምጡ።