የአረቡ ዓለም መነሣሣትና አብዮቶች በኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ምሁር ዐይን
በቱኒዝያ የሥራ አጥነት ችግርና አገሪቱ ውስጥ እየተንሠራፋ የሄደው ሙስና ያስቆጣው ሕዝብ ለ 23 ዓመታት ሥልጣን ላይ በኃይል የቆዩትን ፕሬዘዳንት ቤን አሊን ካባረረ እነሆ ዓመት ሊሆነው ነው። ያ ክስተት በአካባቢው ለሚገኙ አምባገነን መንግሥታት ቆፍጣና መልዕክት ማስተላለፉ ይታመናል።
ቱኒዝያ ውስጥ እራሡን መስዋዕት ባደረገ አንድ ዜጋ አነሣሽነት የተቀጣጠለው ሕዝባዊ ዓመፅ በበርካታ የአረብ ሀገሮች ተስፋፍቶ ግብጽን፥ ሊቢያን፥ የመንን፣ ባሕሬንና ሦሪያን አዳርሷል።
ሀገሮቹ ባሁኑ ወቅት በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? ወዴትስ እያመሩ ነው?
ስለ አካባቢው ሁኔታ በቅርብ የሚከታተሉ የፖለቲካ ሣይንስ ምሁር ጋብዘናል። አቶ ጃዋር መሐመድ ይባላሉ። ሰሎሞን ክፍሌ ነው ያወያያቸው።
በቱኒዝያ ቤን አሊ ከተባረሩ በኋላ በሀገሪቱ ከትላንት ዛሬ የተሻለ ነገር ይታያል ወይ? ሲል ላስቀደመው ጥያቄ መልስ በመስጠት ይጀምራሉ።
ቃለ ምልልሱን ያዳምጡ፡፡