ከአብን ሰልፍ ጋር በተያያዘ በእስር የነበሩ ሰዎች እየተለቀቁ ነው

ለረቡዕ ጥቅምት 18/2013 ዓ.ም ጠርቶ ከነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ የታሰሩ ግለሰቦች እንዳሉ ያረጋገጡት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ አሁን ግን እየተለቀቁ ነው ብለዋል። ሰልፍ በተጠራበት ቀን እንወጣለን ያሉ ጥቂት ወጣቶች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው ታስረው ነበር ነው ያሉት።

ሰልፉን የጠራው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን/ የታሱሩ አባላቱ እየተፈቱ መሆኑን ጠቅሷል የተያዙት ግን በቢሮ ውስጥ እንዳሉ እንጅ ሰልፍ ወጥተው አይደለም ብሏል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

Your browser doesn’t support HTML5

ከአብን ሰልፍ ጋር በተያያዘ በእስር የነበሩ ሰዎች እየተለቀቁ ነው