የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጉባዔ ተጠናቀቀ

  • እስክንድር ፍሬው

ብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን)

ዛሬ ስብሰባውን ያጠናቀቀው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ ደመቀ መኮንንን ሊቀመንበር፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር በማድረግ በድጋሚ መርጧል፡፡

ዛሬ ስብሰባውን ያጠናቀቀው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ ደመቀ መኮንንን ሊቀመንበር፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር በማድረግ በድጋሚ መርጧል፡፡ በገጠሙን ችግሮችና በመንስዔቻቸው እንደዚሁም በመፍትሄው ላይ የሃሳብ አንድነት መምጣቱ፣ የስብሰባው ስኬት ነው ብለዋል፡፡ የብአዴን ማዕከላዊ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለምነው መኮነን፡፡

በቅርቡ በሚካሄደው ጉባዔ ለኢህአዴግ ሊቀመንበርነት ብሎም ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ብአዴን ዕጩ ያቀርብ እንደሆን ተጠይቀው፣ ዕጩ የማግኘቱ ጉዳይ በተናጠል በአንድ ፓርቲ ሳይሆን፣ በኢህአዴግ በአጠቃላይ በጋራ የሚወሰን ነው ብለዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጉባዔ ተጠናቀቀ