በኢትዮጵያ እስር ቤት የሚገኙት የግንቦት ሰባት ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ በተሻለ ሁኔታ መያዛቸዉን የአገሪቱ ዉጭ ግዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገለጹ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በኢትዮጵያ እስር ቤት የሚገኙት የግንቦት ሰባት ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ በተሻለ ሁኔታ መያዛቸዉን የአገሪቱ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገለጹ።
ሚኒስትሩ ትላንት ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዩ የአማርኛዉ ቋንቋ ስርጭት ስለ ፕሬዚደንት ኦባማ ኢትዮጵያ ጉብኚት በሰጡት ቃለ ምልልስ ስለ አቶ አንዳርጋቸዉ አያያዝ ተጠይቀዉ ፣ ታሳሪዉ በመኪና ሆነዉ አገሪቱ በልማት እያደረገች ያለችዉን ግስጋሴ እንዲጎበኙ ሁሉ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
አቶ አንዳርጋቸዉ ፍርድ ፊት ለመቅረብ ፣ የህግ ጥብቅና ለማግነትና በቤተሰብ ለመጎብኘትስ ችለዋል ወይ ስንል ላቀረብንላቸዉ ጥያቄ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ የሚከተለዉን መልሰዋል።
የእንጊሊዝ ዜግነት ያላቸዉ የግንቦት ሰባት ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ከአንድ ዓመት በፊት ሰኔ 2006 ዓም የመን ዉስጥ በኢትዮጽያ ጸጥታ ሃይሎች ተይዘዉ መወሰዳቸዉ ይታወሳል። ከዚያን ጊዜ ወዲህ ሁለት ጊዜ ብቻ በኢትዮጵያ የእንጊሊዝ ኤምባሳ ባለስልጣናት እንደተጎበኙ ተገልጿል። የብሪታኒያ መንግስት በቅርቡ ባወጣዉ መግለጫ የዜጋዉ የአንዳርጋቸዉ ጽጌ ጉዳይ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባለዉ ግንኙነት አሉታዊ እንደምታ እንዳያስከትል መናገሩ አይዘነጋም።
Your browser doesn’t support HTML5