ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ደ’ኤታ አቶ ታየ ደንዳኣን ከሥልጣን በማንሣት ለእስር መዳረጋቸው፣ “በፓርቲውም ኾነ በመንግሥታቸው ውስጥ የሚነሣን ተቃውሞ እንደሚሰጉ ያሳያል፤” ሲሉ፣ ነዋሪነታቸውን በአሜሪካ ያደረጉት የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል አመራር ዶክተር ሚልኬሳ ሚዳጋ ተናገሩ፡፡
SEE ALSO: የአቶ ታዬ ደንዳአ ቤተሰቦች ከመኖሪያ ቤታቸው እንዲወጡ መደረጋቸውን ገለጹለአገሪቱ የሰላም ዕጦት መንግሥትን ተጠያቂ ያደረጉት አቶ ታየ፣ ጦርነት እንዲቆምና ዕርቅ እንዲደረግ በመናገራቸው ከሥልጣናቸው እንደተነሡ፣ ከእስሩ አስቀድመው ገልጸዋል፡፡ የፌደራል የጸጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኀይል ግን፣ መንግሥትን ለመጣል ከሽብር ቡድኖች ጋራ በኅቡእ ያሴራሉ፤ በማለት በቁጥጥር ሥር እንዳዋላቸው ይፋ አድርጓል፡፡
የሕግ ባለሞያ የኾኑት አቶ ዳንኤል ውብሸት ደግሞ፣ ለእስሩ የቀረቡ መንግሥታዊ ክሶች፣ “አሳማኝ ያልኾኑና ሒደቱም የሕዝብ ተመራጩን ያለመከሰስ መብት የጣሰ ነው፤” ሲሉ ይተቻሉ፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
Your browser doesn’t support HTML5