በአምስት ዓመታት ውስጥ ዝቅተኛ የተባለው የዋጋ ንረትና የባለሞያዎች አስተያየት

ፎቶ ፋይል፡ መርካቶ፣ አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ኅዳር ወር መጨረሻ የተመዘገበው የዋጋ ንረት 16.9 በመቶ መኾኑን ገልጾ፣ “ይህም ባለፉት አምስት ዓመታት ከተመዘገበው ዝቅተኛው ነው” ሲል ትላንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ባንክ አዲስ የተቋቋመው የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ የመጀመርያ ስብሰባን ተከትሎ በአወጣው መግለጫ ለዚህ ውጤት መገኘት ደግሞ የተከተለው ጥብቅ የገንዘብ ቁጥጥር ፖሊሲ ዋና ምክንያት መሆኑን ገልጿል።

Your browser doesn’t support HTML5

በአምስት ዓመታት ውስጥ ዝቅተኛ የተባለው የዋጋ ንረትና የባለሞያዎች አስተያየት

የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የፋይናስ ባለሞያዎች በበኩላቸው መንግሥት አሁንም የዋጋ ንረቱን ከዚህም በላይ ዝቅ ለማድረግ መሥራት ይኖርበታል ብለዋል። ባለሞያዎቹ፣ “የዋጋ ግሽበት እየቀነሰ ነው ማለት ኑሮ እየረከሰ ነው ማለት አይደለም” ብለዋል። በዚኽ ዙሪያ የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።