ትንታኔ:- በኢራን ኒዩክሌር ፕሮግራም ዙሪያ የተደረሰው “ታሪካዊ” ስምምነትና አንድምታው፤

Your browser doesn’t support HTML5

ትንታኔ:- በኢራን ኒዩክሌር ፕሮግራም ዙሪያ የተደረሰው “ታሪካዊ” ስምምነትና አንድምታው፤

ኢራንን የኒዩክሌር ጦር መሳሪያ ባለቤት ከመሆን ለማገድ የታለመና በአጻፋውም በቴሕራን ላይ የተጣለውን ማዕቀብ የሚያነሳ ስምምነት በሳምንቱ መጀመሪያ በቪየና ጸድቋል።

ለርካታ ዓመታት በኢራንና ምዕራባውያን መካከል የነገሰ ውጥረት፤ ሁለት ዓመታት የዘለቀ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት፤ ታሪካዊ መሆኑ በተነገረለት ባለ ብዙ ፈርጅ ስምምነት ይደምደም እንጂ ከተግባራዊነቱ እስከ እድሜ የጠገቡ ጥርጣሬዎችና ሥጋቶቹ አሁንም በሥፋት እያነጋገረ ይገኛል።

ለመሆኑ ስምምነቱ ምን ዓይነት ተጨባጭ ውጤት ያፈራ ይሆን?

ስምምነቱ በሁለቱ ቁልፍ አገሮች ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን በየፊናቸው የሚጠብቁት ፈተናዎችና የመጨረሻ እጣውስ?

የባለ ሞያ ትንታኔ ይዘናል።

ዶ/ር ሹመት ሲሻኝ በቨርጂኒያው የክርስቶፈር ኒውፖርት ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምሕር ናቸው። በዘመናዊ የመካከለኛው ምሥራቅና የእስልምና ጉዳዮች ዙሪያ ጥናቶች ያደርጋሉ።

ሙሉውን ቃለ ምልልስ ከዚህ ያድምጡ፤