የርዕሰ ብሄር ህገ መንግሥታዊ ሥልጣን ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችና የባለሙያ ምላሽ

የቀድሞ ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘወዴና አዲስ የተሾሙት አምባሳደር ታየ አጥቀስላሴ

Your browser doesn’t support HTML5

የርዕሰ ብሄር ህገ መንግሥታዊ ሥልጣን ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችና የባለሙያ ምላሽ

በኢትዮጵያ ርዕሰ ብሄር በሚመረጥበት ወቅት ከሚነሱት ጉዳዮች አንዱ ከርዕሰ ብሄሩ ሥልጣንና ተግባር ጋር በተያያዘ በህገ መንግሥቱ የተቀመጡ ድንጋጌዎች ይገኙበታል፡፡

“እነዚህ ድንጋጌዎች ማሻሽያ ያስፈልጋቸዋል” በሚል ጥያቄዎች ሲነሳባቸው መቆየቱን የሚናገሩት በዚህ ዙሪያ የሚነሱትን አበይት ጉዳዮች ጨምረው የሚያስረዱት የህገ መንግሥትና ሰብዓዊ መብቶች ባለሙያው አቶ በላቸው ግርማ ናቸው። ፕሬዘዳንት የሚመረጥበትን ሂደት በተመለከተም ድንጋጌዎቹ ግልጽነት ይጎድላቸዋል ይላሉ፡፡